am_jer_tn/09/04.txt

42 lines
3.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ከኤርምያስ ጋር መነጋሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "እናንተ እያንዳንዳችሁ",
"body": "“እናንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡"
},
{
"title": "ከጎረቤቶቻችሁ ተጠብቀቁ፣ በወንድሙም ላይ አይታመን",
"body": "“አብረዋችሁ ያሉትን እስራኤላውያንን ከማመን ተጠንቀቁ፣ የራሳችሁን ወንድም ቢሆንም አትመኑ”"
},
{
"title": "እያንዳንዱ ጎረቤት በሐሜት ይመላለሳል",
"body": "እዚህ ላይ “ይመላለሳል” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን መኖርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ጎረቤት አንዱ ሌላውን ያማል” ወይም “እያንዳንዱ ጎረቤት ሐሜተኛ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እያንዳንዱ ሰው በጎረቤቱ ላይ ያፌዛል፣ እውነትን ደግሞ አይናገርም",
"body": "“ሁሉም ሰዎች እርስ በርሳቸው ያፌዛሉ፣ እውነትን ደግሞ አይናገሩም”"
},
{
"title": "ምላሶቻቸው ሐሰተኛ ነገሮችን ያስተምራሉ",
"body": "እዚህ ላይ ለንግግራቸው አጽንዖት ለመስጠት ሲባል ሰዎች “በምላሶቻቸው” ተወክለዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሐሰተኛ ነገሮችን ያስተምራሉ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክፉንም በማድረግ ደክመዋል",
"body": "“ብዙ ኃጢአት በማድረግ ደክመዋል”"
},
{
"title": "መኖርያችሁ በሽንገላ መካከል ነው",
"body": "እግዚአብሔር በውሸታሞች መካከል መኖር በሽንገላ መካከል መኖር እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መኖርያችሁ በውሸታሞች መኖርያ መካል ነው” ወይም “እናንተ የምትኖሩት በውሸታሞች መካከል ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሽንገላቸው",
"body": "“እነዚህን ሁሉ ውሸቶች በመናገር”"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]