am_jer_tn/09/01.txt

54 lines
4.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔርና ኤርምያስ ስለ ይሁዳ ሕዝብ መነጋገር ቀጥለዋል፡፡"
},
{
"title": "ምነው ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዓይኖቼ የውሃ መጉረፊያ በሆኑልኝ!",
"body": "ይህን የሚናገረው ኤርምያስ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ኤርምያሰ ምን ያህል እያለቀሰ እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የበለጠ እንባ ማፍሰስ ብችል እመኝ ነበር” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቀንና ሌሊት",
"body": "“ቀን” እና “ሌሊት” የሚሉትን በመጥቀስ ይህ ሀረግ ሁልጊዜ የሚል ትርጉም ይኖረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ” ወይም “ያለማቋረጥ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሕዝቤ ሴት ልጅ",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር እንደ ሴት ልጅ በመግለጽ ለእነርሱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል፡፡ እዚህ ላይ ኤርምያስ እግዚብሔር የተጠቀመበትን ተመሳሳይ ሀረግ ሕዝቡን ለመግለጽ ይጠቀማል፡፡ ይህንን በኤርምያስ 4፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የእግዚአብሔር ሴት ልጅ የመሰሉትን ሕዝቤ” ወይም “ውድ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የተገደሉትን",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላት የገደላቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንድ ሰው ቢሰጠኝ ኖሮ",
"body": "“አንድ ሰው ቢሰጠኝ ኖሮ እመኝ ነበር፡፡” አሁንም የሚናገረው ኤርምያስ ነው፡፡"
},
{
"title": "በምድረ በዳ ለሚጓዙ መቆያ የሚሆን ስፍራ",
"body": "ይህ የሚወክለው በምድረ በዳ ለሚጓዙ ሰዎች ከጉዞአቸው ቆመው ሌሊቱን ተኝተው የሚያሳልፉበትን ሕንጻ ነው፡፡ "
},
{
"title": "ሕዝቤን ትቼ",
"body": "“ሕዝቤን ተውኋቸው”"
},
{
"title": "የአታላዮች መንጋ",
"body": "“ሌሎች ሰዎችን የሚያታልሉ የሰዎች ስብስብ”"
},
{
"title": "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል",
"body": "“ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው” የሚለውን በኤርምያስ 1:8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡"
},
{
"title": "ሐሰትን ለመናገር ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ",
"body": "ውሸትን መናገር በክፉዎች ምላስ እንደሚሰራ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪ የተነገረ ውሸት ወደኋላ መመለስ ስለማይቻል ውሸትን መናገር ቀስትን እንደ መወርወር ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ቀስትን የሚጠቀሙ ሰዎች የቀስቱን ገመድ ለማሰር ቀስታቸውን መያዝ አለባቸው፣ ስለዚህ እዚህ ላይ ውሸታሞች ምላሳቸውን በመጠቀም ምላሳቸውን እንደሚገትሩ ተደርገው ተጠቅሰዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውሸታቸው በምላሳቸው እንደሚወረወር ቀስት ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ነገር ግን በምድር የበረቱት በታማኝነታቸው ምክንያት ፈጽሞ አይደለም",
"body": "“በምድር የበረቱት ለእግዚአብሔር ታማኞች በመሆናቸው ምክንያት አይደለም፣ እነርሱ ክፉዎች ናቸውና” እና “ይህ ማለት ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች አይደሉም ማለት ነው፣ ነገር ግን እንዲያውም እነርሱ ክፉዎች ናቸውና ኃይላቸውን ያገኙት በክፋታቸው ነው” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከአንድ የክፋት ተግባር ወደ ሌላ የክፋት ተግባር ይሄዳሉ",
"body": "አንድን ክፉ ተግባር ከሌላው ክፉ ተግባር ቀጥሎ ስለመፈጸም ሲናገር ክፉ አድራጊዎች ከአንድ ድርጊት ወደ ሌላ ድርጊት እንደሚሄዱ ተደርጎ ተገልጦአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገሮችን በማድረግ ቀጥለዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]