am_jer_tn/08/20.txt

26 lines
2.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "ኤርምያስ ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "“እኛ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታል፡፡ “እኔ” እና “የእኔ” የሚሉት ቃላት ኤርምያስን ያመለክታሉ፡፡"
},
{
"title": "መከሩ አልፎአል",
"body": "“የመከር ጊዜ አልፎአል”"
},
{
"title": "ነገር ግን እኛ አልዳንንም",
"body": "ኤርምያስ የይሁዳ ሕዝብ የሚናገሩትን ያስተላልፋል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እግዚአብሔር እኛን አላዳነንም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔም ተሰብሬአለሁ፣ ጠቁሬማለሁ፡፡ በእርስዋ ላይ በሆኑት አስከፊ ነገሮች እኔ አዝኛለሁ፤ እኔ ተስፋ ቆርጫለሁ",
"body": "እነዚህ ዓረፍተ ሃሳቦች አጽንዖት ለመስጠት ከአንድ በላይ መንገድ በመጠቀም ተመሳሳይ ሃሳብ ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?",
"body": "እነዚህ ጥያቄዎች የጠጠየቁት የይሁዳ ሕዝብ እንዳልዳኑ ዋናውን ነጥብ ለማስተላለፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በገለዓድ መድኃኒት አለ፣ በዚያ ሐኪሞች አሉ፣ ስለዚህ የውድ ሕዝቤ ፈውስ ለምን እንደማይከናወን ንገሩኝ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]