am_jer_tn/08/16.txt

54 lines
3.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለሚመጣው ቅጣት መልእክቱን ቀጥሏል፡፡ "
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “የእርሱ” እና “እነርሱ” የሚሉት ቃላት የይሁዳ ጠላቶችን ያመለክታል፡፡"
},
{
"title": "የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የፈረሶቹን ፉርፉርታ የዳን ሕዝብ ሰምተውታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፌርፉርታ",
"body": "ፈረስ በአፍንጫው የሚያሰማው ከፍ ያለ ድምጽ"
},
{
"title": "ፈረሶች",
"body": "ጎልማሳ ወንዶች ፈረሶች"
},
{
"title": "ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች",
"body": "ይህ ግነት ሲሆን የይሁዳ ሕዝብ በፍርሃት ለመንቀጥቀጣቸው ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የምድሪቱ ሕዝቦች በሙሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ” (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በጠንካራ ፈረሶቹ የማሽካካት ድምጽ",
"body": "“የጠላትን ጠንካራ ፈረሶች ድምጽ በሰሙ ጊዜ”"
},
{
"title": "ማሽካካት",
"body": "ፈረስነየሚያሰማው ድምጽ"
},
{
"title": "እነርሱ ይመጡና ይውጡአችኋል",
"body": "እዚህ ላይ “ይውጡአችኋል” የሚለው ቃል መብላት ማት ነው፡፡ ይህ ጠላቶች እንዴት እንደሚመጡና ምድሪቱንና በእርሷ የሚኖሩትን ሰዎች እንደሚያጠፉ የሚያሳይ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ይመጡነና ያጠፉአችኋል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተመልከቱ",
"body": "“አሁን አስተውሉ”"
},
{
"title": "እኔ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦች፣ በአስማት ብልሃት ልትከለክሉአቸው የማትችሉአቸውን እፉኝቶች እልክባችኋለሁ",
"body": "እባቦቹና እፉኝቶቹ የጠላትን ወታደር ይወክላሉ፣ መንከሳቸው ደግሞ የጠላትን ጥቃት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በመካከላችሁ ከቁጥጥራችሁ በላይ የሆኑ የጠላት ወታደሮችን እልካለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በአስማት ብልሃት ልትከለክሉአቸው የማትችሉአቸውን እፉኝቶች",
"body": "እዚህ ላይ አስማት ማድረግ የሚለው ሀረግ እባቦችን ለመቆጣጠር መዘመር ወይም ሙዚቃ ማሰማት ነው፡፡ "
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]