am_jer_tn/08/14.txt

38 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "የይሁዳ ሕዝብ በሚቀጡበት ጊዜ ምን እንደሚሉ ለእኛ በመንገር እግዚአብሔር መልእክቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "“እኛ”፣ “ለእኛ” እና “የእኛ” የሚሉት ቃላት የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታሉ፡፡ "
},
{
"title": "ለምን እዚህ እንቀመጣለን?",
"body": "ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የድርጊት እርምጃን ለማነሳሳት ነው፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እዚህ መቆየት የለብንም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በአንድነት ወደዚህ ኑ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሂድ",
"body": "`የተመሸጉ ከተሞች” ከፍተኛ የግንብ አጥር እና ጠንካራ ከለላ የነበራቸው ከተሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ተመሳሳይ ሀረጎች በኤርምያስ 4:5 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸቸው ተመልከት፡፡ "
},
{
"title": "በዚያ እንሞታለን፣ ድምጻችንንም እናጠፋለን",
"body": "እዚህ ላይ “ድምጻችንንም እናጠፋለን”የሚለው መሞት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እዚያ እንሙት” ወይም “በዚያ እንዲገድሉን ጠላቶቻችንን እንጠብቅ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል",
"body": "እዚህ ላይ “እንድንጠፋ” የሚለው የሞት ፍርድ እንደተላለፈባቸው የሚያሳይ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አምላካችን የሞት ፍርድ ስላስተላለፈብን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መርዝ እንድንጠጣ ያደርገናል",
"body": "ይህ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ያስተላለፈውን ፍርድ የሚያሳይ ፈሊጥ ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን መልካም ነገር አይኖርም",
"body": "“ነገር ግን አንድም መልካም ነገር አይሆንም”"
},
{
"title": "ነገር ግን ተመልከቱ",
"body": "“ነገር ግን አስተውሉ”"
}
]