am_jer_tn/08/11.txt

50 lines
4.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች “እነርሱ”፣ የእነርሱ” እና ለእነርሱ” የሚሉት ቃላት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡"
},
{
"title": "የሕዝቤን ቁስል በጥቂቱ ይፈውሳሉ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ቁስል ከኃጢአታቸው የተነሳ የሚገጥማቸውን ችግር የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ችግር ቀለል እንደሆነ ያስባሉ” ወይም 2) ቁስል የሕዝቡን ኃጢአት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ኃጢአት እንደ ትንሽ ቁስል ቀላል እንደሆነ ያስባሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቁስልን በጥቂቱ ይፈውሳሉ",
"body": "እዚህ ላይ “ጥቂት” የሚለው ቃል ቁስል ቀላል እንደሆነና ብዙ አስቸጋሪ እንዳልሆነ አድርገው በማየት ተገቢ እንክብካቤ አለመስጠትን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰላም ሳይሆን ‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ",
"body": "“‘ሁሉም ደህና ነው፣ ሁሉም ደህና ነው’ ይላሉ፣ ነገር ግን ደህና አይደለም” "
},
{
"title": "አስጸያፊ ነገሮችን ሲሰሩ አፍረዋልን?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በኃጢአታቸው ባለማፈራቸው ምክንያት ቁጣውን ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም አስደንጋጭ ኃጢአት ሰርተዋል፣ ነገር ግን ምንም አያፍሩም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንዴት ማፈር እንዳለባቸው አያውቁም",
"body": "“ፊታቸው እንኳ ፈጽሞ አልቀላም፡፡” ሰው ሲያፍር ብዙ ጊዜ ፊቱ ይቀላል፡፡ "
},
{
"title": "ከሚወድቁት ጋር ይወድቃሉ",
"body": "እዚህ ላይ “ይወድቃሉ” የሚለው ይገደላሉ የሚለውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተገደሉት ከሌሎቹ ጋር አብረው አንድ ላይ ይገደላሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ",
"body": "እዚህ ላይ “ይዋረዳሉ” የሚለው መጥፋትን ይወክላል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በምቀጣቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ቅጠሉ ይረግፋል",
"body": "“ቅጠሉ ይደርቃል”"
},
{
"title": "እኔ የሰጠኋቸው ሁሉ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል",
"body": "እዚህ ላይ የመጀመርያው ጽሑፍ ትርጉም ምን እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡"
}
]