am_jer_tn/08/08.txt

70 lines
5.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ "
},
{
"title": "“ጥበበኞች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ ከእኛ ጋር ነው” እንዴት ትላላችሁ?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው የይሁዳ ሕዝብ ምን እየተናገሩ እንደነበር እንዲያስቡ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ጥበበኞች እንደሆናችሁ ታስባላችሁ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሕግ ከእናንተ ጋር በመኖሩ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እናንተ እንዴት ትላላችሁ",
"body": "“እናንተ” የሚለው የይሁዳ ሕዝብን ይወክላል፡፡"
},
{
"title": "በእርግጥ፣ ተመልከቱ!",
"body": "እነዚህ ቃላቶች አድማጩ ለሚቀጥለው መልእክቶች የቅርብ ትኩረት እንዲሰጥ የሚናገር ነው፡፡"
},
{
"title": "የጸሐፊዎቻችሁ ሐሰተኛ እስክርቢቶ",
"body": "እስክርቢቶ ጸሐፊዎች የሚጽፉአቸውን ቃላት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጸሐፊዎቻችሁ የሚጽፉአቸው የሐሰት ነገሮች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሐሰትን ፈጥረዋል",
"body": "“ሐሰተኛ ሃሳቦች ለእናንተ ሰጥተዋል”"
},
{
"title": "ጥበበኛ ሰዎች ያፍራሉ",
"body": "ይህ ምጸት ነው ምክንያቱም ጥበበኞች ሰዎች ሁልጊዜ ስለ ጥበባቸው ይከበራሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ጥበበኞች እንደሆኑ የሚያስቡ ሰዎች ሃፍረት ይሰማቸዋል” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ደንግጠዋል",
"body": "ፈርተዋል ወይም ተርበድብደዋል"
},
{
"title": "እነሆ!",
"body": "“ትኩረት ስጡ!"
},
{
"title": "ስለዚህ ጥበባቸው ምን ይጠቅማቸዋል?",
"body": "ይህ ጥያቄ አሉታዊ መልስ ይጠብቃል፤ ዓላማውም አድማጮቹ የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው እያሉ እነርሱ ጥበብ ብለው የሚናገሩት በእርግትም ጠቃሚነቱ ምን ያህል ትንሽ እንደሆነ እንዲያስቡት ለመማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ጥበብ ነው ብለው የሚያስቡት ነገር ምንም መልካም ነገር አይሰራላቸውም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ስስታሞች ናቸው!ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና",
"body": "ይህን በኤርምያስ 6:13 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልክት᎓᎓"
},
{
"title": "ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስታሞች ናቸው!",
"body": "“ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ” የሚለው ሀረግ የይሁዳ ሕዝብ በሙሉ ያለ ምንም የማንነትና የኑሮ ደረጃ ልዩነት “ሁሉ” በሚለው ቃል ውስጥ መካተታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ምክንያቱም ስልጣን ያላቸው፣ ስልጣን የሌላቸውና ሌሎቹንም እያንዳንዳቸውን ጨምሮ ሁሉም ስስታሞች ናቸው” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ታናሹ",
"body": "ይህ ከፍተኛ ስፍራ የሌላቸውና በሰው እይታ ግምት ውስጥ የማይገቡ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ዝቅተኛ ስልጣን ያላቸው” (የስም ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ታላቁ",
"body": "ይህ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸውንና በሰው ዘንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ሰዎች” ወይም “ከፍተኛ ኃይል ያላቸው ሰዎች” (የስም ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሁሉም",
"body": "“የይሁዳ ሕዝብ በሙሉ”"
},
{
"title": "ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ሲሉ ስግብግብ ናቸው",
"body": "“ጥቅም” የሚለው ረቂቅ ስም “የበለጠ ገንዘብ ማግኘት” ወይም “የበለጠ ቁሳቁስ ለማግኘት” በሚሉት ሀረጎች ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች ውሸት በመናገር ብዙ ገንዘብ ያገኛሉ” ወይም “ብዙ ቁሳቁስ ለማግኘት በብርቱ ይፈልጋሉ፣ እነዚህን ለማግኘት ደግሞ ሰዎችን ያታልላሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሁሉም ያጭበረብራሉ",
"body": "“ሁሉም ሰዎችን ያታልላሉ” ወይም “ሁሉም ውሸታሞች ናቸው”"
}
]