am_jer_tn/08/04.txt

30 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ለእነርሱ” እና “እነርሱ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ "
},
{
"title": "ለእነርሱ እንዲህ በላቸው",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ምን መናገር እንዳለበት ለኤርምያስ እየነገረው ነው፡፡"
},
{
"title": "የወደቀ ሰው አይነሳምን? የሳተስ ሰው ለመመለስ አይሞክርምን? ታዲያ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ባለመታመን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላው ይመለሳል? ",
"body": "እነዚህ ጥያቄዎች የይሁዳ ሕዝብ ይኖሩበት የነበረው መንገድ ትርጉም የሚሰጥ እንዳልሆነ ዋነኛ ነጥቡን በሚገባ ግልጽ አድርገዋል፡፡ እነዚህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ሲወድቅ እንደገና ሊነሳ እንደሚችል፣ አንድ ሰው ከመንገድ ሲስት እንደገና ወደ መንገዱ ለመመለስ እንደሚሞክር ታውቃላችሁ፡፡ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ባለመታመን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላው መሄዱ ትርጉም የማይሰጥ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ኢየሩሳሌም",
"body": "እዚህ ላይ “ኢየሩሳሌም” የሚለው ቃል የይሁዳን ሕዝብ በሙሉ ወካይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይሁዳ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተንኮልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል",
"body": "የይሁዳ ሕዝብ ይሰሩት የነበረው ነገር ተንኮልን አጥብቀው እንደያዙና ሊተዉት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተንኮልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል",
"body": "“ተንኮል” የሚለው ረቂቅ ስም ሰው ሊይዘው የሚችለው አንድ ግዑዝ ቁስ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ “አታለለ” በሚለው ግስ በመጠቀም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አንድን ነገር የሙጥኝ ብሎ መያዝ ለመውደድ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሚያታልላቸው ነገር ነገር ለመመለስ እምቢ አሉ” ወይም “የሚያታሉሏቸውን ሰዎች ወደዱ” (ረቂቅ ስሞች እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]