am_jer_tn/08/01.txt

58 lines
4.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "በዚያን ጊዜ",
"body": "በኤርምያስ 7:32 እስከ 34 ውሰጥ ያሉት ክስተቶች በሚፈጸሙበት ጊዜ፡፡"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እነርሱ ያመጡአቸዋል",
"body": "እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የይሁዳን ሕዝብ ጠላቶች ይወክላል፡፡"
},
{
"title": "መኳንንቶቻቸው ",
"body": "“ነገስታቶቻቸው” ወይም “መሪዎቻቸው”"
},
{
"title": "እነርሱን ይዘረጉአቸዋል",
"body": "“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በቀደመው ጥቅስ የተዘረዘሩትን ሰዎች አጥንቶች ነው፡፡"
},
{
"title": "እነርሱ በተከተሏቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም አብረው በተጓዟቸውና በፈለጓቸው፣ ባመለኳቸው",
"body": "እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን የሚያመለክት ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡"
},
{
"title": "አብረው በተጓዟቸው",
"body": "ይህ ለማገልገልና ለማምለክ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 2:23 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አጥንቶች አይሰበሰቡም ወይም እንደገና አይቀበሩም",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አጥንቶቻቸውን ማንም ሰው አይሰበስበውም ወይም እንደገና አይቀብሯቸውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ተጣለ ጉድፍ በምድር ገጽ ላይ ይበተናል",
"body": "አጥንቶች በምድር ላይ ካለ ጉድፍ ተነጻጽረዋል፣ ይህ ንጽጽር አጥንቶቹ አስጸያፊ እንደሚሆኑና እንደገና እንደማይቀበሩ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምድረ ገጽ ላይ",
"body": "“በምድር ዙርያ ሁሉ”"
},
{
"title": "እነርሱን ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ",
"body": "“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳ ሕዝብን ነው፡፡"
},
{
"title": "ከዚህ ክፉ ሕዝብ አሁንም የቀሩት ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ለራሳቸው ሞትን ይመርጣሉ",
"body": "“ከዚህ ክፉ ሕዝብ የቀሩት ሁሉ በሕይወት ከሚኖሩ መሞት ይፈልጋሉ”"
},
{
"title": "ይህ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው ",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ተመሳሳይ ቃላትን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]