am_jer_tn/07/31.txt

50 lines
3.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ የሰራቸውን ክፉ ነገሮች መግለጹን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እነርሱ” እና “የእነርሱ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ "
},
{
"title": "የቶፌት ከፍተኛ ስፍራዎች",
"body": "ይህ የእስራኤል ሕዝብ ልጆቻቸውን በእሳት በማቃጠል ለሐሰተኛ አማልክት መስዋዕት አድርገው ያቀረቡበት የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የቤን ሄኖም ሸለቆ",
"body": "ይህ ሕዝቡ ለሐሰተኛ አማልክት መስዋዕት ያቀረቡበት ከኢየሩሳሌም ከተማ በደቡብ በኩል የሚገኝ የሸለቆ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእሳት",
"body": "ይህ አመልካች መረጃ ለሐሰተኛ አማልክት እንደ መስዋዕት ይቃጠሉ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ መስዋዕት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከቶ በአእምሮየ ያለሰብሁትን",
"body": "እዚህ ላይ “አእምሮ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ሃሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከቶ ስለዚህ ነገር ፈጽሞ አላሰብሁም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህ ተመልከቱ",
"body": "እዚህ ላይ “ተመልከቱ” የሚለው ቃል ለሚከተለው ነገር አጽንዖትን ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርግጥ”"
},
{
"title": "የማይባልበት ቀናቶች ይመጣሉ",
"body": "የወደፊት ጊዜ “ቀናቶች እየመጡ እንደሆነ” ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለወደፊት እንዲህ የማይባልበት” ወይም “እንዲህ የማይባልበት ጊዜ ይኖራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ከእንግዲህ ወዲህ … ተብሎ አይጠራም",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ከእንግዲህ እንዲህ … ብለው አይጠሩትም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አስከሬኖች ይቀብራሉ",
"body": "“የሞቱ ሰዎችን ይቀብራሉ”"
},
{
"title": "የሚቀር ምንም ክፍል የለም",
"body": "“የሚቀር ምንም ቦታ የለም”"
}
]