am_jer_tn/07/27.txt

26 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ያለውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ለእነርሱ” እና “እነርሱ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ "
},
{
"title": "ስለዚህ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለእነርሱ ትናገራለህ ነገር ግን አንተን አይሰሙህም፡፡ እነዚህን ነገሮች ለእነርሱ ትናገራለህ ነገር ግን ለአንተ አይመልስሉህም፡፡",
"body": "እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ሃሳብ አላቸው፣ ሁለተኛው ለመጀመርያው መልእክት አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔን መልእክት ንገራቸው ነገር ግን እነርሱ አንተን አይሰሙህም ለአንተም አይመልሱልህም” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የአምላኩ የእግዚአብሔር ድምጽ",
"body": "እዚህ ላይ “የአምላኩ የእግዚአብሔር ድምጽ” የሚለው እግዚአብሔር የተናገረውን ይወክላል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡25 ላይ እንዴት እንደተረገምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አምላኩ እግዚአብሔር የተናገረው ነገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ እውነት ሲናገር ሕዝቡ ሊያጠፉት የሚችሉትና መነገሩንም ሊያስቆሙት የሚችሉት ነገር እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቡ እውነትን አጥፍተዋል፣ ከአፋቸውም ቆርጠውታል” ወይም “ሕዝቡ ውሸት ብቻ ይናገራሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እውነት ጠፍቶአል",
"body": "“እውነት” የሚለው ረቂቅ ስም “እውነተኛ” በሚለው ቅጽል በመጠቀም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እውነተኛ የሆነው ነገር ጠፍቶአል” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]