am_jer_tn/07/24.txt

38 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ያለውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ “እነርሱ” የይሁዳ ሕዝብ አባቶችን የሚያመለክት ነው፡፡ "
},
{
"title": "እነርሱ አይሰሙም ወይም ትኩረት አይሰጡም",
"body": "እነዚህ ሀረጎች የሚናገሩት ስለ አንድ ነገር ነው፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት",
"body": "“በራሳቸው እቅድ ምክንያቱም ክፉና እልኸኞች ነበሩ”"
},
{
"title": "ወደፊት ሳይሆን ወደኋላ ሄዱ",
"body": "ይህ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እርሱን በጉጉት ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ትኩረት ለመስጠት እምቢተኞች ሆኑ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ እኔ ከመቅረብ ይልቅ ከእኔ ርቀው ሄዱ” ወይም 2) ከማሻሻል ይልቅ በክፋታቸው እየጨመሩ ሄዱ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተሻሉ ከመሆን ይልቅ በክፋታቸው እየጨመሩ ሄዱ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ",
"body": "ይህ ጅምላ ገለጻ ሲሆን ሃሳቡም በዚህ የጊዜ ርዝመት በየቀኑ ለማለት ሳይሆን በጥቅሉ በዚህ ሁሉ የጊዜ ርዝመት ለማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ” (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱን በቋሚነት ልኬባችኃለሁ",
"body": "“እነርሱን ደጋግሜ ልኬአቸዋለሁ” ወይም “እነርሱን በተደጋጋሚ ልኬአቸዋለሁ”"
},
{
"title": "እነርሱ አንገታቸውን አደነደኑ",
"body": "ይህ ፈሊጥ ሲሆን ግትሮች ነበሩ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግትሮች ሆኑ” ወይም “እኔን ተቋቋሙኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የባሰ ክፉ ነበሩ",
"body": "“እያንዳንዱ ትውልድ የበለጠ ክፉ ነበረ”"
}
]