am_jer_tn/07/21.txt

26 lines
2.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ያለውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም ጠቃሚ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 6:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ "
},
{
"title": "የሚቃጠለውን መስዋዕታችሁን በሌሎች መስዋዕታችሁ ላይ ጨምሩ፣ ስጋውንም ራሳችሁ ብሉ",
"body": "ይህ መስዋዕታቸው በሙሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አጽንዖት የሚሰጥ ምጸታዊ ዓረፍተ ሃሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሂዱና የሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁን ከመስዋዕታችሁና ከስጋው ጋር አብራችሁ ብሉት” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ድምጼን ስሙ",
"body": "እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ቃሉን መስማትና ለተናገረው ደግሞ መታዘዝ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተናገርሁትን ስሙ ደግሞም ታዘዙ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ",
"body": "እግዚአብሔር ቃሉን ስለመታዘዝ ሲናገር ሰው በመንገድ እንደሚሄድ እንደዚሁ አንድ ሰው በቃሉ መሄድ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ አድርጉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]