am_jer_tn/07/19.txt

50 lines
3.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ለኤርምያስ መናገር ቀጥለሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች “እነርሱ” እና “ራሳቸው” የሚሉት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ "
},
{
"title": "በእውነት እነርሱ እኔን ያስቆጡኛልን?",
"body": "ይህ ጥያቄ አሉታዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ በእርግጥ ሊያስቆጡኝ አይችሉም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "ኤርምያስና የይሁዳ ሕዝብ እርሱ የሚናገረውን ነገር በጥንቃቄ ይሰሙ ዘንድ እግዚአብሔር ስለራሱ ሲናገር ሌላ ሰው እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህንን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያወጀው ይህን ነው” ወይም “ “እግዚአብሔር የተናገረው ይህን ነው” (ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እፍረታቸው በራሳቸው ላይ ይሆን ዘንድ እኔን ያስቆጡኝ አነርሱ ራሳቸው ኤደሉምን?",
"body": "ይህ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እፍረታቸው በራሳቸው ላይ ይሆን ዘንድ ራሳቸውን እያስቆጡ ነው” ወይም “እነርሱ ራሳቸውን ችግር ውስጥ እያስገቡና በራሳቸው ላይ እፍረት እያመጡ ነው!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እፍረት በእነርሱ ላይ ነው",
"body": "“እፍረት” የሚለው ረቂቅ ስም “አፈሩ” በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አፈሩ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተመልከት",
"body": "ይህ ቃል እዚህ ላይ የአንድ ሰውን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚነገረው ቁም ነገር ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድምጥ” ወይም “እኔ ለአንተ ለምነግርህ ነገር ትኩረት ስጥ” "
},
{
"title": "ቁጣየና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይጎርፋል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ቁጣው ሲገልጽ ሊፈስ የሚችል ነገር እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ይህን ስፍራ እቀጣለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቁጣና መዓት",
"body": "እነዚህ ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይነት ያላቸው ሲሆኑ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጥልቀት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አጎርፋለሁ",
"body": "“አፈስሳለሁ”"
},
{
"title": "ይነድዳል ደግሞም አይጠፋም",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ቁጣው ሲናገር ቁጣው ሊጠፋ የማይችል እሳት እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቁጣየን አንድም ሰው ሊያስቆመው አይችልም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፈጽሞ አይጠፋም",
"body": "“ፈጽሞ መንደድ አይቆምም”"
}
]