am_jer_tn/07/12.txt

30 lines
2.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚያስተላልፈውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት “እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡"
},
{
"title": "በቀድሞ ዘመን ስሜ እንዲያድርበት ወደፈቀድሁበት በሴሎ ወደነበረው ስፍራ ሂዱ",
"body": "እዚህ ላይ “ስሜ እንዲያድርበት ወደፈቀድሁበት” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ይህ ስፍራ እግዚአብሔር ይመለክበት የነበረ ነው የሚል ትርጉም አለው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀድሞ ሕዝቤ እኔን ለማምለክ እኔ ወደፈቀድሁበት በሴሎ ወዳለው ስፍራ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስላደረጋችሁ",
"body": "“ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስታደርጉ ስለነበራችሁ”"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እንደገና ደግሜ ደጋግሜ",
"body": "እነዚህ ሁለት የተጣመሩ ስሞች ፈሊጥ ሲሆኑ አንድ ነገር ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ተደርጓል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተደጋጋሚ” ወይም “ያለማቋረጥ” (ጥምር ቃል እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ በስሜ የተጠራው ቤት",
"body": "ይህ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምትክ ስም ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይሀንን በኤርምያስ 7፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ የሆነው ይህ ቤት” ወይም “እኔን የምታመልኩበት ይህ ቤተ መቅደስ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]