am_jer_tn/07/08.txt

54 lines
5.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚነገረውን መልእክቱን ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታል፡፡"
},
{
"title": "እነሆ!",
"body": "እዚህ ላይ “እነሆ” የሚለው ቃል ከዚህ በኋላ የሚከተለውን መረጃ እንደሚገባ ልብ እንድንል ያነቃናል፡፡"
},
{
"title": "ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ? በሐሰትም ትምላላችሁ፥ … የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ?",
"body": "እየፈጸሟቸው ያሉትን ኃጢአቶች እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ እንደ አረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፡፡ በሐሰት ትምላላችሁ፥ … የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሐሰት ትምላላችሁ",
"body": "“በመኃላችሁ እንኳ ትዋሻላችሁ”"
},
{
"title": "እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ",
"body": "እዚህ ላይ መከተል ለማገልገልና ለመታዘዝ ዓላማ በማድረግ ተከትሎ ለመሄድ ምትክ ስም ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 7:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች አማልክት ታገለግላላችሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ታዲያ መጥታችሁ በፊቴ ትቆሙና … እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ታደርጋላችሁ?",
"body": "በቃልና በድርጊት የሚፈጽሙትን ግብዝነት እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ እንደ አረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደዚያ ከሆነ መጥታችሁ በፊቴ ትቆማላችሁ … እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ታደርጋላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በስሜ በሚጠራው ቤት",
"body": "ይህ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ የሆነው ቤት” ወይም “እኔን የምታመልኩበት ቤተ መቅደስ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ በስሜ የሚጠራው ቤት በእናንተ ዓይን የወንበዴዎች ዋሻ ሆኖአልን?",
"body": "እነርሱ ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምን እንደሚያስቡ እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ በዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስሜን የተሸከመው ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የወንበዴዎች ዋሻ ነው!” ወይም “በስሜ የተጠራው ይህ ቤት ወንበዴዎች ሊሔዱና ሊሸሸጉ የሚችሉበት ስፍራ እንደሆነ የምታስቡ ትመሰስላላችሁ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስሜን የተሸከመው ይህ ቤት",
"body": "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔርን ስም እንደተሸከመ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ ከዚህ በፊት ካው ጥቅስ “በስሜ በተጠራው ይህ ቤት” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወንበዴዎች",
"body": "የሚሰርቁና የሚዘርፉ ሃይለኛ ሰዎች"
},
{
"title": "ነገር ግን እነሆ አይቻለሁ",
"body": "“ነገር ግን እኔ በእርግጠኝነት እናንተ የምትሰሩት ምን እንደሆነ ተመልክቻለሁ”"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]