am_jer_tn/07/03.txt

26 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚነገረውን መልእክቱን ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም ጠቃሚ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 6:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ "
},
{
"title": "መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ እኔም እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ",
"body": "“መንገዳችሁንና ሥራችሁን የምታስተካሉ ከሆነ እኔም እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ "
},
{
"title": "በዚህ ስፍራ",
"body": "ይህ በይሁዳ ምድር ማለት ነው፣ በቤተ መቅደስ አይደለም"
},
{
"title": "እያላችሁ ራሳችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ",
"body": "ይህ “ራሳችሁ” የሚለው ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም ለእስራኤላውያን ወደፊት የሚመጣ የግል አደጋ እንዳለ አጽንዖት የሚሰጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያላችሁ፣ እናንተን እንዲጠብቃችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ” (ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ!የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ! የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ! ",
"body": "ቤተ መቅደሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር ስለሆነና የእርሱን ሕልውና የሚወክል ስለሆነ እርሱ ይጠብቀዋል፣ የይሁዳም ሕዝብ ደህንነት ይሆንለታል፡፡ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” የሚለው ለምን ሦስት ጊዜ እንደተደጋገመ ተቀባይነት ሊኖራቸው የሚችሉት ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፡- 1) የተደጋገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው ወይም 2) የተደጋጋመው እንደ ቤተ መቅደሱ ስነ ስርአት ተደርጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው ስለዚህ አንድም ሰው ሊያፈርሰው እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ነን፤ እኛ ደግም እንጠበቃለን፡፡” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]