am_jer_tn/04/30.txt

50 lines
4.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ "
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ሴተኛ አዳሪ እንደነበሩ አድርጎ ይናገራቸዋል ምክንያቱም እነርሱ ሌሎች አማልክትን በማምለክ ለእርሱ ታማኞች ስላልነበሩ ነው፡፡"
},
{
"title": "አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፣ አሁን ምን ትሰሪያለሽ?",
"body": "ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ራሳቸውን ለመርዳት ሊያደርጉት የሚችሉት ምንም ነገር እንደሌለ ለእስራኤል ሕዝብ ለመንገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አሁን ጠላቶቻችሁ ለጥፋት ዳርገዋችኋል፣ እርዳታ ለማግኘት ልታደርጉ የምትችሉት ምንም ነገር የለም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቀይ ለበስሽ … በወርቅ አጌጥሽ … ዓይኖችሽን … በኵል ተኳልሽ ",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሲናር ወንዶችን ወደራሷ ለመማረክ ራስዋን እንደምታስውብ ሴተኛ አዳሪ እንደነደበሩ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ሴተኛ አዳሪ ቀይ ለበስሽ … በወርቅ አጌጥሽ … ዓይኖችሽን … በኵል ተኳልሽ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቀይ ልብስ ለበስሽ",
"body": "እዚህ ላይ “ቀይ” የሚለው ውድ የሆነ ቀይ ልብስን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውድ የሆነ ቀይ ልብስ ለበስሽ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ራስሽን በወርቅ ጌጣጌጥ አጌጥሽ",
"body": "“የወርቅ ጌጣጌጥ አደረግሽ”"
},
{
"title": "የተወዳጀሻቸው ወንዶች አሁን ትተውሻል",
"body": "እግዚአብሔር ይሁዳ ለባለጠግነትና ለንግድ ስለተማመነችባቸው መንግስታት ሲናገር ይሁዳን እንደተወዳጁ ወንዶች አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ እነዚህ መንግስታት የእግዚአብሔርን ፍርድ ሲመለከቱ ይሁዳን ይተዉአታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ሕይወትሽን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው",
"body": "እዚህ ላይ “ሕይወትሽን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው” የሚለው የይሁዳን ሕዝብ ለመግደል እየሞከሩ መሆናቸውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አንቺን ለመግደል እየሞከሩ ነው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በወሊድ እንደምትጨነቅ",
"body": "ይህ ተነጻጻሪ ዘይቤ ጥቅም ላይ የዋለው ይሁዳ ምን ያህል ክፉኛ እንደምትጨነቅ ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሴት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ የሚሰማት ዓይነት ሕመምና ስቃይ ከባድ ጭንቀት” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የጽዮን ሴት ልጅ ",
"body": "እግዚአብሔር ስለ እነርሱ እንደ ሴት ልጁ አድርጎ በመናገር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ፍቅሩን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውድ ሴት ልጄ፣ ጽዮን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወዮልኝ",
"body": "“እኔ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነኝ”"
},
{
"title": "ተዝለፈለፍሁ",
"body": "“እኔ እየደከምሁ ነው”"
}
]