am_jer_tn/04/21.txt

22 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እስከ መቼ የጦርነት ዓርማ እመለከታለሁ? እስከ መቼስ የመለከቱን ድምፅ እሰማለሁ?",
"body": "ኤርምያስ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ለዚህ ያህል ረጅም ጊዜ የጦርነት ዓርማ ስለመመልከቱና የመለከቱን ድምፅ ስለመስማቱ ያለውን ጭንቀት ለማሳየት ነው፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት ቢያልቅ ይመኛል፡፡ ይህ በግነት መልክ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጦርነቱ ቢያልቅና የጦርነት ዓርማው ቢወርድ እና የጦር ሰራዊቱ የመለከት ድምጽ ቢቆም እንዴት እመኝ ነበር” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የጦርነት ዓርማ",
"body": "“የጦጦነት ሰንደቅ ዓላማ”"
},
{
"title": "የመለከት ድምፅ ",
"body": "አንድ ሰው ለጦርነት ጥሪ ለማድረግ እንደ ምልክት መለከት ይነፋል፡፡"
},
{
"title": "ሕዝቤ ሰንፈዋልና … በጎ ነገርን ማድረግ አያውቁም",
"body": "እግዚአብሔር እንዲህ እንደተናገረ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ምናልባት እግዚአብሔር ጦርነቱ አሁንም ለምን እየተካሄደ እንደሆነ ለኤርምያስ የሰጠው ምላሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፣ ‘በሕዝቤ ሞኝነት ምክንያት ነው … በጎ ነገርን ማድረግ አያውቁም፡፡’” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሞኝ ሕዝብ",
"body": "“ደደብ ሕዝብ”"
}
]