am_jer_tn/04/19.txt

30 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ልቤ! ልቤ!",
"body": "እዚህ ላይ “ልብ” እንደ ሀዘንና ፍርሃት የመሳሰሉ የሚያሰቃዩ ስሜቶች ይወክላል፡፡ ሀረጎቹ የተደጋገሙት የስቃዩ ጥልቀትን ለመግለጽ ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ በልቤ ጭንቀት አለብኝ",
"body": "ተናጋሪው ከባድ አካላዊ ሕመም የሚያመጣ ከባድ ስሜታዊ ሕመም ተሰምቶታል፡፡"
},
{
"title": "በውስጤ ልቤ ታውኮብኛል",
"body": "“በውስጤ ልቤ ከመጠን በላይ ይመታል፡፡” እዚህ ላይ “ልብ” የሰውነት ክፍልን ያመለክታል፡፡ ልቤ የሚታወከው ከመደበኛው በላይ በጣም ጠንካራና ፈጣን በሆነ መልኩ ስለሚመታ ነው፡፡ "
},
{
"title": "ሁከት",
"body": "ግራ መጋባት፣ አመጽ፣ ወይም ምስቅልቅል የሆነ ነገር የተሞላበት፤ ያልተረጋጋ ወይም ያልሰከነ"
},
{
"title": "በድንገትም ድንኳኔ ጠፉ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች በድንገት ድንኳኔን አፈረሱት” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቅጽበት ዓይን መጋረጃዎቼ ጠፉ",
"body": "“ጠፉ” የሚለው ቃል ከበፊቱ ሀረግ በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መጋረጃዎቼ በቅጽበት ዓይን ጠፉ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መጋረጃዎች",
"body": "መጋረጃዎች በድንኳን ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ለመከፋፈል የሚሰቀሉ ጨርቆች ናቸው፡፡"
}
]