am_jer_tn/04/16.txt

30 lines
3.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ጠባቂዎች ይመጣሉ",
"body": "“ጠባቂዎች” በከተማው የሚኖሩ ሰዎች የምግብና የውኃ አቅርቦት እንዳያገኙ ለመጠበቅ ከተማይቱን የሚከብቡ ወታደሮች ናቸው፡፡"
},
{
"title": "እነርሱ በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ይሆኑባታል",
"body": "ሰዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡና ወደ ውጭ እንዳይወጡ ከተማን በጥንቃቄ መጠበቅ ሰዎች ከእርሻ እንዳይሰርቁ እርሻን በጥንቃቄ እንደሚጠብቁ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተመቻቸ እርሻን በጥንቃቄ እንደሚጠብቁ ጠባቂዎኢየሩሳሌምን በጥንቃቄ ይጠብቁአታል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሷን ዙርያዋን ሁሉ ከብበው",
"body": "“እርሷ” የሚለው ቃል ኤሩሳሌምን ያመለክታል፡፡ ኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ እንደ ሴት እንደሆነች ተደርጋ ትነገራለች፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሷ በእኔ ላይ ዓመፀኛ ነበረች",
"body": "“እርሷ” የሚለው ቃል ኢየሩሳሌምን ያመለክታል፣ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ደግሞ ይወክላል፡፡ “እኔ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኢየሩሳሌም ሕዝብ በእኔ ላይ አመፀኞች ነበሩ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "የገዛ ጠባይሽና ሥራሽ እነዚህን ነገሮች አድርጎብሻል",
"body": "እዚህ ላይ “ጠባይ” እና “ስራ” ነገሮችን ማድረግ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አነዚህ ረቂቅ ስሞች “የሰራችሁት ስራ” በሚለው ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት በሰራችሁት ስራ ምክንያት ነው” (ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ ልብሽን ይሰብራል",
"body": "እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል ምናልባት ስሜትን ያመለክታል፣ “ልብሽን የይብራል” የሚለው ሀረግ ደግሞ ምናልባት በከፋ መልኩ እንዲሰቃዩ ማድረጉን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልብሽን በጥልቀት እንደሚሰብር ይሆንብሻል” ወይም “በጣም አስደንጋጭ በሆነ ጭንቀት እንድትሰቃዪ ያደርግሻል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]