am_jer_tn/04/13.txt

42 lines
4.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ተመልከቱ፣ እርሱ እንደ ደመና ያጠቃቸዋል",
"body": "“እርሱ” የሚለው ቃል ጠላት የሆነውን ንጉስና ጦር ሰራዊቱን ያመለክታል፡፡ የጦር ሰራዊቱ በቁጥር ብዙ መሆን እጅግ በጣም ከባድ የደመና አውሎ ነፋስ እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተመልከቱ፣ እንደ ታላቅ ደመና የሆኑ ብዙ ጦር ሰራዊቶች ለማጥቃት እየተሰባሰቡ ነው” ወይም “ብዙ ጦር ሰራዊቶች ለማጥቃት እየተሰባሰቡ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው",
"body": "የጠላት ሰረገሎች እንደ ዐውሎ ነፋስ እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ ዐውሎ ነፋስ ታላቅ ድምጽ ያላቸው፣ አጥፊና ፈጣን እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚመጡት የሰረገሎቻቸው ጩኸት እንደ አጥፊ ዐውሎ ነፋስ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለእኛ ወዮልን",
"body": "“ይህ አሰደንጋጭ ነው”"
},
{
"title": "መጥፋታችን ነውና",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ያጠፉናልና” ወይም “እነርሱ ያወድሙናልና” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ",
"body": "ይህ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ “ልብሽን እጠቢ” የሚለው ክፋትን ከሕይወታቸው ለማስወገድ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ክፉ መሆን አቁሙ” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ በክፋት መኖር አቁሙ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ኃጢአት እንዴት እንደምትሰሪ ጥልቅ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?",
"body": "ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ሁልጊዜ እንዴት ኃጢአት መስራት እንዳለባቸው ስለማቀዳቸው ሕዝቡን ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእናንተ ጥልቅ ሃሳብ እንዴት ኃጢአት መስራት እንዳለባችሁ ነው” ወይም “ሁልጊዜ ኃጢአት እንዴት መስራት እንዳለባችሁ ታስባላችሁ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )"
},
{
"title": "የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ዘንድ ዜና ያመጣል",
"body": "እዚህ ላይ “ድምፅ” መልእክተኛን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልእክተኛ ይመጣና በዳን ምን እየሆነ እንዳለ ይነግራችኋል” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዳን",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ምናልባት ምዕራባዊ ኢየሩሳሌም የሆነውን የዳን አካባቢ ነው፡፡"
},
{
"title": "ከኤፍሬም ተራሮች የሚመጣው ጥፋት ይሰማል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኤፍሬም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ሰዎች ይሰማሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከዳን … የኤፍሬም ተራሮች",
"body": "ጠላቶች ወደ ዳንና ኤፍሬም እንደደረሱ በመስማት በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ጠላቶች ወደ እነርሱ እየቀረቡ እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡ "
}
]