am_jer_tn/04/09.txt

14 lines
1.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል",
"body": "እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ወኔን ይወክላል፡፡ በተጨማሪ “ልብ ይሞታል” የሚለው ወኔ ማጣትንና መፍራትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ንጉሡና መኳንንቱ ወኔአቸው ይጠፋል” ወይም “ንጉሡና መኳንንቱ ይፈራሉ” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰይፍ በሕይወታቸው ላይ ተቃጥቷል",
"body": "እዚህ ላይ ሕዝቡን ለመግደል ስለተዘጋጁት ጠላቶች ሲናገር ሰይፉ በሰዎች ላይ እንደሚሰነዝር ሰው ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን በሰይፋቸው እኛን ለማረድ ተዘጋጅተዋል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]