am_jer_tn/04/07.txt

34 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አንበሳ እየመጣ ነው",
"body": "እግዚአብሔር በጣም ኃያል ስለሆነ ጦር ሰራዊት ሲናገር በጣም ኃይለኛ ተናካሽ አንበሳ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃይለኛና ምህረት አልባ ጦር ሰራዊት እየቀረበ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ጭፍቅ ዱር",
"body": "ተጠጋግተው አብረው ያደጉ የቁጥቋጦ ክምችት"
},
{
"title": "ሕዝብን የሚያጠፋ አንድ ሰው ",
"body": "እዚህ ላይ “አንድ ሰው” የሚለው ንጉስና ሰራዊቱን የሚወክል ነው፡፡ (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወጥቶአል",
"body": "ይህ ፈሊጥ መንቀሳቀስ መጀመሩን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መዝመት እየጀመረ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድርሽን ባድማ የሚያደርግ",
"body": "ይህ ሰዎች ምድሪቱን ሲመለከቱ ድንጋጤ የሚፈጥርባቸው ዓይነት ጥፋት የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድርሽን ለማጥፋት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማቅ ልበሱ",
"body": "ሰዎች በጣም ኃዘንተኞች እንደሆኑ ለመግለጽ ማቅ ይለብሳሉ፡፡ በዚህ ዓውድ ሕዝቡ ስለሰሩአቸው ክፉ ስራዎች በጣም ማዘናቸውን ለማሳየት ሊሆን ይችላ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማዘናችሁን የሚያሳዩ ልብሶችን ልበሱ” (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዋይ በሉ",
"body": "በከፍተኛ ጩኸት ማልቀስ"
},
{
"title": "የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና",
"body": "“ቁጣ” ከሰዎች ሊመለስ የሚችል ሕይወት ያለው ነገር እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰም” የሚለው እግዚአብሔር አሁንም በሕዝቡ ላይ ተቆጥቷል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አሁንም በሕዝቡ ላይ በጣም ተቆጥቷልና” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]