am_jer_tn/04/04.txt

46 lines
3.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ለእግዚአብሔር ራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ",
"body": "እግዚአብሔር ሕዝቡ ለእርሱ ያለውን ታማኝነት በአካል በሚገለጥ የቃል ኪዳን ምልክት መግለጫ ቋንቋ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አቅርቡ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ራሳችሁን ግረዙ … የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታወነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለተቱም አንድ ላይ ትዕዛዙን አጽንዖት ይሰጡታል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል",
"body": "እግዚአብሔር ከመጠን በላይ ስለመቆጣቱ ሲናገር ቁጣው እሳት እንደሆነ አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቍጣዬ እንደ እሳት ይነድዳል ማንም ሊያጠፋው አይችልም” ወይም “እኔ ከመጠን በላይ እቆጣለሁ እኔን ማቆም የሚችል ማንም የለም” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቁጣ",
"body": "“ታላቅ ንዴት”"
},
{
"title": "በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለቱም በአንድ ላይ ትዕዘዙን አጽንዖት ይሰጡታል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነትየሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች እንዲሰሙት አድርጉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ",
"body": "መለከት ሰዎችን ጠላቶቻቸው ሊያጠቁአቸው እየመጡ እንደሆነ ያስጠነቅቃል፡፡ "
},
{
"title": "ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሂድ",
"body": "እነርሱ ከጠላቶቻቸው ለመዳን ወደ ተመሸጉት ከተሞች ይሄዳሉ፡፡"
},
{
"title": "ክፉ ነገር … ታላቅ ጥፋት",
"body": "እነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ “ታላቅ ጥፋት” የሚለው ሀረግ “ክፉው ነገር” ምን እንደሚሆን ያብራራዋል፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና",
"body": "ይህ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን ለማምጣት ከሰሜን ጦር ሰራዊት እንደሚልክ የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እናንተን እንዲያጠፋ ከሰሜን ጦር ሰራዊት እንዲመጣ አደርጋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከሰሜን",
"body": "ይህ ከሰሜን የሚመጣውን የጠላት ጦር ሰራዊት የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]