am_jer_tn/04/01.txt

42 lines
5.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እስራኤል ሆይ፣ ብትመለስ ",
"body": "እዚህ ላይ “መመለስ” የሚያመልኩትን ለመለወጥ ተለዋጭ ዜቤ ነው፣ እስራኤል ደግሞ የእስራኤልን ሕዝም የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጣዖቶችን ያመልክ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የምትመለስ ከሆነ” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የምታመልከውን የምትለውጥ ከሆነ” ( ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "በመመለስህ ለእኔ ትሆናለህ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ ወደ ማን መመለስ እንዳለባቸው አጽንዖት የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ እኔ ተመለስ” ወይም “እኔን አምልክ” 2) ይህ ሁኔታዎችን የሚያብራራው የመጀመርያው ሀረግ ድጋሚ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ እኔ የምትመለስ ከሆነ” ወይም “እንደገና እኔን ማምለክ የምትጀምር ከሆነ” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ",
"body": "እዚህ ላይ “አስጸያፊ ነገሮች” የሚለው እግዚአብሔር የሚጠላቸው ጣዖቶችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አስጸያፊ ጣዖቶችህን ከእኔ ፊት ብታስወግድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከእኔ ርቀህ መቅበዝበዝ ብትተው",
"body": "እዚህ ላይ “መቅበዝበዝ” የሚለው ታማኝ ላለመሆን ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእኔ ታማኝ ሆነህ ብትቀጥል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሕያው እግዚአብሔር",
"body": "“እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ሕያው እንደሆነ ሁሉ፡፡” ሕዝቡ ይህን መግለጫ የሚጠቀሙት ቀጥለው የሚናገሩት ነገር በእርግጠኝነት እውነት እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ የማይናወጥ ቃል ኪዳን የማድረግ መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በማይናወጥ መልኩ እምላለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ",
"body": "እዚህ ላይ “አሕዛብ” ለሌሎች መንግስታት ሕዝቦች ምትክ ስም ነው፡፡ “እርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ የሚናገረው እግዚአብሔር ስለሆነ “እኔ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሌሎች መንግስታት ሕዝቦች በእኔ ይባረካሉ” (ምትክ ስም እና አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ",
"body": "እዚህ ላይ “በእርሱ ይባረካሉ” የሚለው እንዲባርካቸው እግዚአብሔርን ለመጠየቃቸው ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሌሎች መንግስታት ሕዝቦች እንዲባርካቸው ይጠይቁታል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእርሱ ይከበራሉ",
"body": "“እርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ የሚናገረው እግዚአብሔር ስለሆነ “እርሱ” የሚለው “እኔ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእኔ ይመካሉ” ወይም “እኔን ያመሰግኑኛል” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዕዳሪውን መሬታችሁን እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ",
"body": "እግዚአብሔር ዘር ለመዝራት መሬቱን እንደሚያዘጋጅ ገበሬ አእንደዚሁ ሕይወታቸውን እንዲያዘጋጁ ለሕዝቡ ይነግራቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]