am_jer_tn/02/35.txt

42 lines
3.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ርቋል ",
"body": "እዚህ ላይ ቁጣ ከእስራኤል እንደሚርቅ ሰው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ርቋል የሚለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የነበረውን ቁጣ ማቆሙን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርግጥ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር የነበረውን ቁጣ አቁሟል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ግን በአንቺ ላይ ፍርድን አመጣብሻለሁ",
"body": "እዚህ ላይ “ፍርድ” ቅጣትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እቀጣሻለሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መንገድሽን እንደ ቀላል ነገር እየለዋወጥሽ ለምን ትሮጫለሽ?",
"body": "እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ይገስጻቸዋል ምክንያቱም እነርሱ ለእርዳታ ሲሉ ከአንድ መንግስት ወደ ሌላ መንግስት እየለዋወጡ ሲሄዱ ነበር ነገር ግን ለእርዳታ በእግዚአብሔር ላይ አልተደገፉም፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ቀላል ነገር",
"body": "ያለ ጥንቃቄ ወይም ተገቢ ግንዛቤ"
},
{
"title": "አንቺ ደግሞ በግብጽ ትዋረጃለሸ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግብጽ ታዋርድሻለች”"
},
{
"title": "አንቺ ደግሞ በግብጽ ትዋረጃለሸ",
"body": "የእስራኤል ሕዝብ ያዝናል ምክንያቱም የግብጽ ጦር ሰራዊት እነርሱን ሊታደጋቸው አይችልም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግብጽ ሊታደግሽ ባልቻለ ጊዜ አንቺ ትዋረጃለሽ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አሦር እንዳዋረደሽ",
"body": "“እንዳዋረደሽ” የሚለው ቃል ከበፊቱ ሀረግ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ በአሦር እንደተዋረድሽ” ወይም “አሦር አንቺን እንዳዋረደችሽ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከዚያም ትወጫለሽ",
"body": "“አንቺ ከግብጽ ትወጫለሽ”"
},
{
"title": "እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ",
"body": "ይህ የኃፍረት ምልክት ነው፡፡ (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንቺም በእነርሱ አይከናወንልሽም",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰለዚህ እነርሱ አይረዱሽም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]