am_jer_tn/02/32.txt

38 lines
4.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?",
"body": "“ትረሳለች” የመሚለው ቃል የሁለተኛው ሀረግ አካል ጭምር እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ትረሳለችን፣ ወይስ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ለአንድ ሰው በጣም ጠቃሚ የሆኑትን ነገሮች የማስታወስን ሃሳብ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቆንጆ ጌጥዋን ማድረግ ፈጽሞ እንደማትረሳ፣ ሙሽራ ደግሞ የሰርግ ልብሷን መልበስ እንደማትረሳ ታውቃላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የማይቆጠሩ ቀናቶች",
"body": "“በጣም ረጅም ጊዜ”"
},
{
"title": "ፍቅርን ለመፈለግ መንገድሽን እንዴት ታቀኛለሽ",
"body": "እግዚአብሔር ፍቅርን በመፈለጋቸው ሕዝቡን እያመሰገናቸው ይታያል፣ ነገር ግን ይህ ምፀት ነው፡፡ እርሱ ለእርሱ ታማኞች ባለመሆናቸው በእነርሱ ላይ እንዳዘነ እያሳያቸው ነበር፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፍቅርን ለመፈለግ",
"body": "እግዚአብሔር ሌሎች አማልክትን ስለሚያመልከው ሕዝቡ ሲናገር ለባሏ ታማኝ እንደልሆነችና እንዲወዳት ሌላ ወንድ እነደምትፈልግ ሴት አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለክፉዎች ሴቶች እንኳ መንገድሽን አስተምረሻል",
"body": "እግዚአብሔር ሕዝቡ ምን ያህል ለእርሱ ታማኝነት የጎደላቸው ስለመሆናቸው ሲናገር ለሴተኛ አዳሪዎች እንኳ እንዴት ለባሎቻቸው ታማኝ መሆን እንደሌለባቸውና ሌሎች ወንዶች የእነርሱ ወዳጆች እንዲሆኑ እንዴት መፈለግ እንዳለባቸው የሚያስተምሩ እንደሆኑ አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የንጹሐን ድሆች ሕይወት የሆነው ደም በልብስሽ ላይ ተገኝቶአል ",
"body": "በልብሳቸው የተገኘው ደም ሰዎችን እንደገደሉ ማስረጃ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በልብስሽ ላይ የተገኘው የንጹሐን ድሆች ደም እነርሱን በመግደልሽ ወንጀለኛ እንደሆንሽ ያሳያል” ወይም “የንጹሐን ድሆች ደም በመግደልሽ ወንጀለኛ ነሽ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሕይወት የሆነው ደም ",
"body": "“ሕይወትን የሚወክለው ደም”"
},
{
"title": "እነዚህ ሰዎች በስርቆት ተግባር የተያዙ አልነበሩም",
"body": "እነርሱ ሰዎችን በስርቆት ተግባር ተሰማርተው ይዘዋቸው ቢሆን ኖሮ ሰዎቹን ለመግደል ምክንያት ይሆንላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱ የገደሏቸው ሰዎች ንጹሐን ነበሩ፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ሰዎች የተለያዩ ነገሮች ሲሰርቁ አላገኛችኋቸውም” ወይም “ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ አንድም ነገር ባይሰርቁም እነርሱን ገድላችኋቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]