am_jer_tn/02/29.txt

38 lines
4.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ታዲያ ለምን እኔን ክፋት እንዳደረግሁባችሁ ትከስሱኛላችሁ? በእኔ ላይ ኃጢአት ያደረጋችሁ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፡፡",
"body": "እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው የእስራኤል ሕዝብ ክፉ እንዳደረገባቸው በማሰብ እርሱን መውቀሳቸውን ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤል፣ ምንም እንኳ በእኔ ላይ ኃጢአት ማድረግን ብትቀጥሉም፣ እኔን በጠራችሁ ጊዜ ሳላድናችሁ በመቅረቴ እኔ ትክክል እንዳልሆንሁ አሰባችሁ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ተግሣጽን አልተቀበሉም",
"body": "እዚህ ላይ “ተግሳጽ መቀበል” ከቅጣት መማርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተግሳጽ መማርን አልተቀበሉም” ወይም “እኔ እነርሱን በገሰጽሁ ጊዜ እኔን መታዘዝን ለመማር ፈቃደኞች አልሆኑም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰይፋችሁ እንደሚያጠፋ አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል",
"body": "እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ነቢያቶቻቸውን ስለመግደላቸው ሲናገር ሰይፋቸው ነቢያቶቻቸውን የበላ አንበሳ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ነቢያቶቻችሁን እንደሚያጠፋ አንበሳ በጭካኔ በሰይፋችሁ ገደላችኋቸው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አጥፊ",
"body": "መጠኑ በጣም ሰፊ የሆነ አደጋ የማምጣት ችሎታ ያለው"
},
{
"title": "የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ! ቃሌን አስተውሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል",
"body": "“ይህ ትውልድ” የሚለው ሀረግ ኤርምያስ ይኖር በነበረበት ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ዛሬ የምትኖሩ ሰዎች፣ እኔ እግዚአብሔር ለእናንተ የምናገረውን ቃል አስተውሉ” "
},
{
"title": "በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁባትን? ",
"body": "እዚህ ላይ “ምድረ በዳ” እና “ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር” ለአደጋ ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ አደገኛ እንደሆነ በማሰባቸው እስራኤልን ለመውቀስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለእናንተ እንደ ምድረ በዳ ወይም ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር እንደሆንሁባችሁ አሰባችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )"
},
{
"title": "ሕዝቤስ ስለ ምን “እኛ ተንከራትተናል ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል”?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ ይህን በመናገሩ ሊገስጸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ሕዝቤ ‘መሄድ ወደምንፈልገው መሄድ እንችላለን፣ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔርን አናመልክም’ ብላችኋል፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መንከራተት",
"body": "ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ወይም ስፍራዎች ያለ ምንም ግልጽ ዓላማ ወይም አቅጣጫ መንቀሳቀስ"
}
]