am_jer_tn/02/26.txt

34 lines
4.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰብ ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ጥቅስ የሚያመለክተው የእስራኤልን ልጆች ነው፡፡ ይህን በኤርምያስ 2:4 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤላውያን” ወይም “የእስራኤላውያን ሕዝብ ወገን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በተያዘ ጊዜ",
"body": "ይህ ፈሊጥ አንድ ሰው የሌላውን ሰው ድርጊት ለይቶ ማወቁን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ሲያገኘው” ወይም “አንዳንድ ነገሮች መስረቁን ሰዎች ባወቁ ጊዜ” (ፈሊጥ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነቢያቶቻቸው",
"body": "ይህ ዝርዝር የእስራኤል አካል የሆነ ማንኛውም ሰው እንደሚያፍር ያሳያል፡፡"
},
{
"title": "ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ’ ድንጋዮንም፡- ‘አንተ ወለድኸኝ’ የሚሉ እነዚህ ናቸው",
"body": "እዚህ ላይ “ግንድ” እና “ድንጋይ” የሚሉት ከእንጨትና ከድንጋይ ተቀርታ የተሰሩ ጣዖቶችን የሚወክሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ቀላት ጣዖቱ የተሰራው በተራ ነገሮች ስለሆነ ሊመለኩ የተገባቸው እንዳልሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእንጨት ተቀርጾ ለተሰራው ጣዖት ‘አንተ አባቴ ነህ’ ለተtቀረጸው ድንጋይ ደግሞ ‘አንተ ወለድኸኝ’ የሚሉ እነዚህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ( ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ",
"body": "“ጀርባቸው ወደ እኔ ነው፤ ፊታቸው ግን ወደ እኔ ዘወር አላለም፡፡” ይህ እግዚአብሔርን መተዋቸውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፊታቸውን ከእኔ መለሱ” ወይም “ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ” ወይም “አነርሱ ፈጽመው ተዉኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተነስተህ አድነን",
"body": "ይህንን የተናገሩት ለእግዚአብሔር እንደሆነ ግልጽ መደረግ አለበት፡፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነስተህ አድነን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ታዲያ ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው?",
"body": "እግዚአብሔር በዚህ ጥያቄ አማካይነት ሕዝቡ የሚያመልኩአቸው ጣዖታቱን እንዲረዷቸው ሊጠይቁአቸው እንደሚገባ ያመለክታል፡፡ እርሱ ይህንን ምፀት የተጠቀመው ሕዝቡ ሌሎች ጣዖቶችን በማምለካቸው እርሱ እንዳዘነ ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሊረዷችሁ ለራሳችሁ የሰራችኋቸውን አማልክት ልትጠይቋቸው ይገባል፡፡” ወይም “ሊረዷችሁ ለራሳችሁ የሰራችኋቸውን አማልክት አልጠየቃችኋቸውም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በመከራህ ጊዜ ለያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣ እስቲ ተነስተው ይምጡና ያድኑህ ",
"body": "እግዚአብሔር ሊያመለክት የፈለገው ሐሰተኛ አማልክት የሚያልኩአቸውን ሰዎች ሊረዷቸው ይገባል የሚል ነው፡፡ ሐሰተኛ አማልክት ሰዎችን ሊረዱ እንደማይችሉ ያውቃል፡፡ እርሱ ይህን ሲናገር የእርሱ ሕዝብ ሐሰተኛ አማልክትን በማምለካቸው እንዳዘነ ለማሳየት ምፀት ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመከራችሁ ጊዜ እነርሱ ሊያድኑአችሁ እንደማይችሉ ስለምታውቁ እነርሱን አልጠየቃችሁም” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]