am_jer_tn/02/20.txt

42 lines
4.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ አንቺም። አንቺ ግን “አላገለግልም አልሽ”",
"body": "እዚህ ላይ “ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ” እና “እስራትሽንም ቆርጫለሁ” ከባርነት አርነት እንዳወጣቸው የሚገልጹ ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ በግብጽ ምድር ባሮች ነበሩ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከረጅም ጊዜ በፊት እኔ ከባርነት ነፃ አወጣኋችሁ፣ ነገር ግን አሁንም እኔን ለማምለክ እንቢ አላችሁ!” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እስራት",
"body": "አንድን ሰው ወይም እንስሳ ለማሰር የሚጠቅም ሰንሰለት"
},
{
"title": "ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ እና ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ",
"body": "ለምን እንደተጋደሙ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ “ማመንዘር” ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆነ ሰውን የሚወክል ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች አመንዝራ ሚስት አንቺም ከእኔ ይልቅ ለጣዖቶች በመስገድ እነርሱን አመለክሽ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በታች",
"body": "ከስር"
},
{
"title": "እኔ እንደ ተመረጠች ወይን፣ ፍጹምም ንጹሕ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር ሕዝቡን እርሱ እንደተከለው እንደ ተመረጠ ወይን በከነዓን ታላቅ ሕዝብ አድርጎ እንደሰራው ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሁሉ የተሻለውን የወይን ዓይነት ለመትከል እጅግ በጣም ጥሩ የሆነውን ዘር እንደሚጠቀም ገበሬ፣ እኔ እግዚአብሔር በመልካም አጀማመር እንድትጀምሩ አድርጌ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የተመረጠ ወይን",
"body": "“በጣም ጥሩ ጥራት ያለው ወይን”"
},
{
"title": "ፍጹም ንጹህ ዘር",
"body": "እዚህ ላይ “ንጹህ ዘር” ጥሩ ካልሆነ ዘር ጋር ያልተዳቀለ በጣም ጥሩ ዘር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም ጥሩ ከሆነ ዘር የበቀለ”"
},
{
"title": "ታዲያ አንቺ ብልሹ፣ የማይጠቅም ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ለመለወጡና እንደ ብልሹና የማይጠቅም ወይን ግንድ ለመሆኑ ሕዝቡን ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን አንቺ ብልሹና የማይጠቅም ወይን ግንድ ሆነሽ ተለወጥሽ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል",
"body": "በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሌለው ነገር እንደረከሰ ተደርጎ ይነገራል፡፡ እዚህ ላይ “ረክሰሻል” የሚለው ለእስራኤል ኃጢአት የማያቋርጥ ማሳሰቢያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጢአትሽን እንደ ርኩሰት አይቼዋለሁ” ወይም “ኃጢአትሽ እንደ ርኩሰት ነው፤ በደልሽ ጸንቶ ይኖራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን ተመሳሳይ ሀረግ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]