am_jer_tn/02/18.txt

22 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ስለዚህ አሁን፣ የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?",
"body": "እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ግብጽንና አሦርን አነርሱን እንዲረዱአቸው መጠየቃቸው ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንደማያመጣላቸው ለሕዝቡ ለማስታወስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ግብጽ በመሄድ ከሺሖር ወንዝ ውኃ መጠጣት ወይም ወደ አሦር በመሄድ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውኃ መጠጣት ለእናንተ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )"
},
{
"title": "የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?",
"body": "እነዚህ የግብጽንና የአሦርን ሰራዊት እነርሱን እንዲረዱአቸው ለመጠየቃቸው ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግብጻውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ … አሦራውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሺሖር",
"body": "ይህ ከግብጽጋር የተያያዘ የአንድ ምንጭ ስም ነው፡፡ ምናልባት የአባይ ወንዝ ገባር ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች አባይ ብለው ይጠሩታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሺሖር ምንጭ” ወይም “የሺሖር ወንዝ” ወይም “የአባይ ወንዝ” (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክፋትሽ ይገስጽሻል፣ ክህደትሽ ይቀጣሻል",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ቅጣታቸው የክፉ ስራቸው ውጤት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉና ከዳተኛ ስለሆንሽ እቀጣሻለሁ” (ሰውኛ ዘይቤ እና ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክፉና መራራ ነው",
"body": "እዚህ ላይ “መራራ” የሚለው ቃል “ክፉ” የሚለውን ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም መራራ የሆነ ክፋት ነው” ወይም “እጅግ በጣም ክፉ ነው” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]