am_jer_tn/02/12.txt

26 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ! እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ",
"body": "እግዚአብሔር መለስ ብሎ እዚያ ሆነው እርሱን እንደሚሰሙት አድርጎ ለሰማያት ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር ይህን የሚናገረው እስራኤል የሰራችው ነገር እጅግ በጣም አስደንጋጭ እንደሆነ ለመግለጽ ነው፡፡ (እንቶኔ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ! እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እግዚአብሔር በሰማይ ላይ ለሚገኙ ፍጡራን ይናገራል ወይም 2) እግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆኑ አድርጎ ለራሳቸው ለሰማያት ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ራሱ የሕያው ውኃ ምንጭ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱ ሕያው ውኃ ምንጭ የሆንሁትን እኔን ትተውኛል” ወይም “እንደ ሕያው ውኃ ምንጭ የሆንሁትን እኔን ትተውኛል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ጕድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኛ አማልክት ሲናገር ሰዎች ውኃ ለማግኘት ሲሉ የቆፈሯቸው ጉድጓዶች እንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለራሳቸው እንደቆፈሯቸው ጉድጓዶች ወደ ሐሰተኛ አማልክት ሄደዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ጉድጓዶች",
"body": "ውኃ ለማከማቸት የሚረዱ ጥልቅ ጉድጓዶች"
}
]