am_jer_tn/02/09.txt

38 lines
3.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ስለዚህ ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ",
"body": "እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ እየተናገረ ነው፡፡ "
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተነገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የልጆቻችሁ ልጆች",
"body": "“የወደፊቱ ትውልዳችሁ”"
},
{
"title": "ወደ ኪቲም ጠረፍ ተሻገሩ",
"body": "ኪቲም በምዕራብ እስራኤል ትገኝ የነበረች ደሴት ናት፡፡ አሁን ቆጵሮስ ተብላ ትጠራለች፡፡ በምዕራብ እስራኤል ሩቅ ያሉትን ምድር በሙሉ የሚወከል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ኪቲም ውቅያኖስ በምዕራብ በኩል ሂዱና ተሻገሩ” (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወደ ቄዳርም መልእክተኞች ላኩ",
"body": "ቄዳር ከምስራቅ እስራኤል በኩል በርቀት ለሚገኝ ምድር የተሰጠ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ቄዳር ምድር በምስራቅ በኩል በርቀት ወዳሉት መልእክተኞች ላኩ” (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በውኑ አማልክት … አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሌሎች ሕዝቦች የራሳቸውን አማልክት ማምለክ መቀጠላቸውን ለእስራኤል ሕዝብ ለመንገር ነው፡፡ እነርሱ አማልክቶቻቸውን ለውጠው ሌሎች አማልክትን አላመለኩም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድም ሕዝብ አማልክቱን … አማልክቱን የለወጠ ፈጽሞ እንደሌለ ታያላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ሊረዳቸው ለማይችል ነገር ለወጡ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ በቀጥታ እንደማይናገር አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን፣ እናንተ፣ ሕዝቤ እኔን የክብራችሁን አምላክ ሊረዳችሁ ለማይችል ነገር ለወጣችሁኝ” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክብራቸው",
"body": "ይህ መግለጫ የሚያመለክተው ክቡር የሆነውን ራሱን እግዚአብሔርን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የከበረ አምላካቸውን” ወይም “እኔ፣ የእናንተ የከበርሁ አምላካችሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሊረዳቸው ለማይችል ነገር ",
"body": "እዚህ ላይ ሐሰተኛ አማልክት ሊሰሩት በማይችሉት ነገር ተገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሊረዱ የማይችሉ፣ ሐሰተኛ አማልክት” ወይም “ሊረዱ የማይችሉ አማልክት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]