am_jer_tn/02/07.txt

38 lines
3.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጢአትን አደረጋችሁ የሰጠኋችሁን ምድር ደግሞ በእኔ የተጠላ እንዲሆን አደረጋችሁት!” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሬን አረከሳችሁ",
"body": "እዚህ ላይ “አረከሳችሁ” የሚወክለው ምድሪቱ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዳይኖራት ማድረግን ነው፡፡ ይህንን ያደረጉት በዚያች ምድር ሆነው ጣዖቶችን በሚያመልኩበት ጊዜ በእርሱ ላይ ኃጢአት በማድረጋቸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሬን ኃጢአት በማድረጋችሁ አረከሳችኋት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ ",
"body": "“በኃጢአታችሁ ምክንያት ርስቴን የተጠላ አደረጋችሁት” ወይም “ኃጢአት በማድረጋችሁ ርስቴን ገፊ አደረጋችሁት” "
},
{
"title": "ርስቴ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- \n1) እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ሲናገር እርሱ እንደወረሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ምድር” ወይም\n2) እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ሰጣት ምድር ሲናገር እርሱ ለእነርሱ እንደ ርስት እንደሰጣቸው አድርጎ ይናገራል” አማራጭ ትርጉም፡- “ለእናንተ የሰጠኋችሁ ምድር” ወይም “እንደ ርስት ለእናንተ የሰጠኋችሁ ምድር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ\n"
},
{
"title": "እግዚአብሔር ወዴት አለ?",
"body": "ይህ ጥያቄ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ መፈለጋቸውን ማሳየት ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔርን መታዘዝ እንፈልጋለን!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለ እኔ ግድ የላቸውም",
"body": "“ለእኔ የተሰጡ አልነበሩም” ወይም “እኔን ተዉኝ”"
},
{
"title": "እረኞቹ በእኔ ላይ አመጹብኝ",
"body": "መሪዎቹ እን እረኞች እነርሱን የሚከተሏቸው ሕዝብ ደግሞ እንደ በጎች ተደርገው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መሪዎቻቸው በእኔ ላይ ኃጢአትን አደረጉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከንቱ ነገሮችን ተከትለው ሄዱ",
"body": "እዚህ ላይ “ተከትለው ሄዱ” የሚወክለው መታዘዝ ወይም ማምለክ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከንቱ ነገሮችን ታዘዙ” ወይም “ከንቱ ነገሮችን አመለኩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከንቱ ነገሮች",
"body": "ከንቱ ነገሮች ሰውን መርዳት የማይችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ጣዖቶችን ያመለክታል፡፡ "
}
]