am_jer_tn/02/04.txt

46 lines
5.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ",
"body": "ያዕቆብና እስራኤል ለአንድ ሰው የተሰጡ ሁለት ስሞች ነበሩ፣ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ሀረጎች የሚያመለክቱት ለአንድ የሕዝብ ወገን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ የያዕቆብ ወገኖች ሁሉ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የያዕቆብ ቤት",
"body": "“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የያዕቆብን ወገኖች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የያዕቆብ ወገኖች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት ",
"body": "“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤል አገርና ሕዝብ የሆኑትን የእስራኤልን ወገኖች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤላውያን” ወይም “የእስራኤላውያን ሕዝብ ወገኖች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አባቶቻችሁ እኔን ከመከተል የራቁት፥ የማይጠቅሙ ጣዖቶችን የተከተሉና ለራሳቸውም ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?",
"body": "እርሱ በሕዝቡ ላይ ምንም ዓይነት ክፋት ስላላደረገ ሕዝቡ እርሱን በመተው ጣዖቶችን መከተል አልነበረባቸውም ብሎ ለመናገር እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለአባቶቻችሁ ምንም ዓይነት ክፋት አላደረግሁም፣ ስለዚህ እኔን ከመከተል ርቀው መሄድ አልነበረባቸውም፣ የማይጠቅሙ ጣዖቶችን ተከትለው መሄድ አልነበረባቸውም፡፡ ይህንን በማድረጋቸው እነርሱ ራሳቸው የማይጠቅሙ ሆኑ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔን ከመከተል ርቀው ሄዱ",
"body": "ይህ የሚወክለው እግዚአብሔርን መተውና ለእርሱ ታማኝ ለመሆን እምቢተኛ መሆንን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እኔን ትተውኛል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የማይጠቅሙ ጣዖቶችን ተከትለው ሄዱ",
"body": "ይ የሚወክለው ለጣዖቶች ታማኝ መሆንንና እነርሱን ማምለክ መምረጥን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማይጠቅሙ ጣዖቶችን አመለኩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የማይጠቅሙ ጣዖቶች",
"body": "ሰዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ነገር ግን ምንም ዓይነት መልካም ነገር የማያመጡላቸው ጣዖቶች፡፡ ትርጉሙ ጠቃሚ የሆኑ አንዳንድ ጣዖቶች እንዳሉ ሰዎች እንዲያስቡ የሚያደርግ መሆን የለበትም፡፡ "
},
{
"title": "አላሉም",
"body": "ይህ በክፍሉ የተገለጸውን መናገር ይኖርባቸው እንደነበር የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲህ ማለት ነበረባቸው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር … ወዴት አለ?",
"body": "ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ጥቅም ላይ መዋል ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያስፈልገናል፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣን እርሱ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በማይኖርበት … የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? ",
"body": "ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ጥቅም ላይ መዋል ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያስፈልገናል፡፡ በማይኖርበት … የመራን እግዚአብሔር እርሱ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድርቅና ጥልቅ ጨለማ ያለበት ምድር",
"body": "“ድርቅ ያለበት ምድር” በቂ ውኃ የሌለበት ምድር ነው፡፡ እዚሀ ላይ “ጥልቅ ጨለማ” ለአደጋ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቂ ውኃ የሌለበት አደገኛ ምድር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]