am_jer_tn/02/01.txt

42 lines
4.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ ሂድ",
"body": "ይህ ፈሊጥ ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በ ኤርምያስ 1:4 ላይ ተመሳሳይ ቃላት እንዴት እንደተረጎምኻቸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለኝ፡- ‘ሂድ’” ወይም “እግዚአብሔር ይህን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡- ‘ሂድ’” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር",
"body": "“ሂድና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ስፍራ ተናገር”"
},
{
"title": "ስለ አንቺ አስባለሁ",
"body": "“ስለ አንቺ አስታውሳለሁ”"
},
{
"title": "በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን የቃል ኪዳን ታማኝነት፣ ፍቅርሽንም",
"body": "“ታማኝነት፣” ወጣትነት፣” እና “ፍቅር” የሚሉት ረቂቅ ስሞች “ታማኝ” እና “ወጣት፣” በሚሉት ቅጽሎች እና “መውደድ” በሚለው ግስ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወጣት በነበርሽ ጊዜ፣ ለቃል ኪዳናችን እንዴት ታማኝ እንደነበርሽ፣ እና እንዴት እንደወደድሽኝ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእጮኝነት ጊዜአችን",
"body": "እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ሲገልጽ ሁለቱ ለመጋባት ተጫጭተው እንደነበር አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁለታችን እንድንጋባ በመጀርያ በተስማማንበት ጊዜ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዘር ባልተዘራበት ምድር",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንም ሰው ዘር ባልዘራበት ምድር” ወይም “ምንም ዓይነት የምግብ ዘር ባልበቀለበት ምድር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የመከሩ በኩራት ነበረች",
"body": "እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሲገልጽ ለእግዚአብሔር የተበረከተች ስጦታ እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ እርሱ መከር በኩራት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከመከሩ በኵራት የበሉት ሁሉ እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ",
"body": "እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ጥቃት ስለፈጸሙት ሲናገር ለእግዚአብሔር ብቻ የተለየውን መስዋዕት እንደበሉ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእስራኤል ላይ ጥቃት የፈጸሙ በሙሉ ከመከሩ በኵራት እንደበሉ ሕዝብ በበደላቸው ተጠይቀዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ክፉ ነገር በእነርሱ ላይ መጣባቸው",
"body": "“በእነርሱ ላይ መጣባቸው” የሚለው ሀረግ በእነርሱ ላይ ሆነ ለሚለው ሃሳብ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገር በእነርሱ ላይ ሆነ” ወይም “እኔ በእነርሱ ላይ አሰቃቂ ነገር እንዲሆንባቸው አደረግሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የተናገረው ቃል በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ለመግለጽ ስለ ራሱ በስሙ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ))"
}
]