am_jer_tn/01/15.txt

34 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እግዚአብሔር ከሰሜን ስለሚመጣው ክፉ ነገር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "ሁሉ",
"body": "ይህ ጅምላ ፍረጃ በሰሜናዊ ክፍል ያሉትን መንግስታት ነገስታትን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ንጉስ” ወይም “የሰሜናዊው ክፍል ነገስታት በሙሉ” (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በኢየሩሳሌም በር መግቢያ ዙፋኑን ያስቀምጣል",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ የሚወክለው በኢየሩሳሌም ላይ መግዛትን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም በር መግቢያ ላይ ይገዛል” ወይም 2) ይህ የሚወክለው በኢየሩሳሌም ላይ መፍረድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም ላይ ይፈርዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በዙሪያዋ በቅጥርዋ ሁሉ ላይ",
"body": "“በዙሪያዋ በቅጥርዋ ሁሉ ላይ” ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ የሚለው በኢየሩሳሌም ዙርያ ያለውን ቅጥርዋን ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ዙርያ ያለውን ቅጥር ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ ይሰጣሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ",
"body": "“በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ” ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ የሚለው የይሁዳ ከተሞችን ሁሉ ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ ",
"body": "“እነርሱን እንዴት እንደምቀጣ እናገራለሁ”"
},
{
"title": "ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ ",
"body": "“በይሁዳ ሕዝብ ላይ ፍርድን እናገራለሁ”"
},
{
"title": "በእጃቸው ለሰሩአቸው ስለ ሰገዱ",
"body": "ሕዝቡ ጣዖታቱን በራሳቸው እጆች ስለሰሩአቸው፣ ጣዖታቱ ሊሰገድላቸው የሚገቡ እንዳልሆኑ ሊያውቁ ይገባቸው ነበር"
}
]