am_jer_tn/01/13.txt

18 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል … እያለ ወደ እኔ መጣ",
"body": "ይህ “የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ” የሚለው ፈሊጥ ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በ ኤርምያስ 1:4 ላይ ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፣ ለውጥ የሚያስፈልግ ከሆነ ለውጥ አድርግ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ” ወይም “እግዚአብሔር ይህንን ሁለተኛ መልእክት ለእኔ ተናገረኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ላይ ላዩን የሚፈላ ",
"body": "ላይ ላዩን የሚለው የሚያመለክተው በማሰሮ ውስጥ ያለውን የውኃው የላይኛውን ክፍል ነው፡፡ ኤርምያስ ውኃው ሲፈላ ማየት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውኃው የሚፈላ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አፉ ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ",
"body": "ይህ ማሰሮው ወደ ሰሜን ማለትም ኤርምያስ ወደ ነበረበት ወደ ይሁዳ ያዘነበለ ነው ማለት ነው፡፡ "
},
{
"title": "ከሰሜን ወገን ክፉ ነገር ይገለጣል",
"body": "“ክፉ ነገር ከሰሜን በኩል ይወርድባቸዋል፡፡” ይህ የሚወክለው እግዚአብሔር ከሰሜን ወደ ደቡብ ክፉ ነገር እንደሚያመጣ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገር ከሰሜን ይመጣል” ወይም “እኔ ከሰሜን ክፉ ነገር እልካለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]