am_jer_tn/01/11.txt

22 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የእግዚአብሔር ቃል ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ",
"body": "ይህ ፈሊጥ ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በ ኤርምያስ 1:4 ላይ ተመሳሳይ ቃላት እንዴት እንደተረጎምኻቸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለ፡- ‘ምን’” ወይም “እግዚአብሔር ይህንን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡- ‘ምን’” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የለውዝ ቅርንጫፍ አያለሁ አልሁ",
"body": "እግዚአብሔር ለኤርምያስ መንፈሳዊ ራዕይ አሳየው፡፡"
},
{
"title": "የለውዝ ቅርንጫፍ ",
"body": "የለውዝ ዛፍ የለውዝ ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ ነው፡፡ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁ",
"body": "ይህ የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚፈጽመው ዋስትና መስጠቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እፈጽመው ዘንድ ቃሌን አስባለሁ” ወይም “እኔ የተናገርሁትን እንደምፈጽመው ዋስትና እሰጣለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቃሌ እተጋለሁ",
"body": "“ለውዝ” እና “እተጋለሁ” የሚሉት የዕብራይስጡ ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን በእርግጠኝነት እንደሚፈጽም ኤርምያስ እንዲያስብ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ "
}
]