am_jer_tn/01/09.txt

30 lines
3.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከዚያም እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ እግዚአብሔርን የሚወክል ተለዋጭ ዘይቤ ሲሆን ለኤርምያስ የመናገር ልዩ ስልጣን መስጠቱን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያም እግዚአብሔር አፌን እንደ ዳሰሰኝ ሆኖ ተሰማኝ” ወይም 2) ኤርምያስ ራዕይ እያየ ነበርና እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ለኤርምያስ የመናገር ልዩ ስልጣን እንደሰጠው ለማሳየት ምሳሌአዊ ድርጊት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያም እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምሳሌያዊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ",
"body": "ይህ ሀረግ እግዚአብሔር ለኤርምያስ መልእክቱን መስጠቱን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሕዝቡ ትናገር ዘንድ እኔ መልእክቴን ለአንተ ሰጥቼሃለሁ” ወይም “ለሕዝቡ መልእክቴን እንድትናገር አስችየሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ … ሾሜሃለሁ",
"body": "ኤርምያስ የእግዚአብሔር መልእክቶች እንደሚፈጸሙ ለተለያዩ መንግስታት በመናገር እነዚህን ነገሮች ይሰራል፡፡ "
},
{
"title": "ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ ",
"body": "አንዳንድ መንግስታትን ይነቅላል፣ ያፈርሳል፣ ያጠፋል ደግሞም ይገለብጣል፣ ሌሎች መንግስታትን ደግሞ ይሰራል እንዲሁም ይተክላል፡፡"
},
{
"title": "መንቀል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ኤርምያስ ሲናገር መንግስታቱ ተክሎች እንደሆኑና እርሱ ከመሬት ነቅሎ እንደሚጥላቸው አድርጎ በመግለጽ በሚናገረው ቃል መንግስታትን እንደሚያፈርስ ይናራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማጥፋት እና መገልበጥ",
"body": "እነዚህ ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ኤርምያስ እነዚህን ቃላት የተጠቀመው ይህ ቃል በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ለማሳየት ነው፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መስራት እና መትከል",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ኤርምያስ ሲናገር መንግስታት እንደ ሕንጻ እንደሆኑና እርሱ እንደሚገነባቸው፣ እንደ ተክሎች እንደሆኑና እርሱ እንደሚተክላቸው በዚህም ጠንካራ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]