am_jas_text_ulb/05/16.txt

2 lines
916 B
Plaintext

\v 16 እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
\v 17 ነቢዩ ኤልያስ እንደኛው ያለ ሰው ቢሆንም፣ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፡፡ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ያህልም ዝናብ አልነበረም፡፡ \v 18 ከዚያም ዝናብ እንዲዘንብ እግዚአብሔርን እየለመነ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዝናብን ላከ፣ ተክሎችም ዐደጉና ሰብልን ሰጡ፡፡