am_jas_text_ulb/05/01.txt

1 line
467 B
Plaintext

\c 5 \v 1 እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስለሚመጡባችሁ ክፉ ነገሮች አልቅሱ ዋይ ዋይም በሉ። \v 2 ሀብታችሁ ሻግቶአል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። \v 3 ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም እናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል። ለመጨረሻው ቀን ሀብታችሁን አከማችታችኋል።