\v 3 ፈረሶች አፍ ውስጥ ልጓም ብናደርግ ይታዘዙልናል፤ መላ አካላቸውንም መቆጣጠር እንችላለን። \v 4 ምንም እንኳ መርከቦች ግዙፍና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም፣ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንደሚመራቸው አስተውሉ።