am_jas_text_ulb/02/21.txt

1 line
593 B
Plaintext

\v 21 አባታችን አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅን መሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ ጸድቆ አልነበረምን? \v 22 እምነት በሥራው ታየ፤ በዚያው ሥራ እምነት ዓላማውን ፈጸመ። \v 23 “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ። ስለዚህም አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። \v 24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን፣ በሥራ እንደሚጸድቅ ታያለህ።