am_jas_text_ulb/02/01.txt

1 line
903 B
Plaintext

\c 2 \v 1 ወንድሞች ሆይ፤ ለአንዳንዶች አድልዎ እያደረጋችሁ የክብር ጌታ የጌታችን አየሱስ ክርስቶስን እምነት እንከተላለን አትበሉ። \v 2 የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰ ወደ ስብሰባችሁ ሲገባና እንዲሁም አዳፋ ልብሶች የለበሰ ድኻ ቢገባ \v 3 ትኵረታችሁ የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰው ሰው ላይ ይሆንና፣ “እዚህ ደኅና ቦታ ላይ ተቀመጥ” ትሉታላችሁ፤ ድኻውን ግን፣ “እዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ \v 4 ታዲያ፣ በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን፤ ደግሞስ በክፉ ዐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን?