am_jas_text_ulb/01/22.txt

1 line
612 B
Plaintext

\v 22 ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ። \v 23 ማንም ቃሉን እየሰማ ቃሉ የሚለውን ባያደርግ፣ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይሆናል። \v 24 ፊቱን አይቶ ይሄዳል፤ ምን እንደሚመስል ግን ወዲያው ይረሳዋል። \v 25 ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።