Mon Sep 19 2016 15:13:39 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2016-09-19 15:13:39 +03:00
parent d773ca0827
commit 475a95060b
5 changed files with 15 additions and 1 deletions

3
05/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\c 5 \v 1 እንግዲህ በክርስቶስ ለማያምኑና ለሚጨቁኑዋችሁ ባለ ጠጎች የምነግራቸው ነገር አለ! እናንተ ባለ ጠጎች ሆይ፥ አድምጡኝ! አሳዛኝ በሆኑ ችግሮች ውስጥ የምታልፉ ስለ ሆናችሁ ልታነቡና ጮኽ ባለ ድምፅ ልታለቅሱ ይገባል!
\v 2 ሀብታችሁ የበሰበሰ ያህል ጥቅም-የለሽ ነው፡፡ የተዋበው ልብሳችሁ በብል የተበላ ያህል ጥቅም-የለሽ ነው፡፡
\v 3 ወርቃችሁና ብራችሁ የዛገ ያህል ጥቅም-የለሽ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሚፈርድባችሁ ጊዜ ይህ ጥቅም-የለሽ ብልጽግናችሁ ስግብግብ መሆናችሁን ይገልጣል፤ ደግሞም ዝገትና እሳት ነገሮችን እንደሚያወድሙ እግዚአብሔር በከባድ ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡ እግዚአብሔር በሚቀጣችሁ ጊዜ እናንተ በከንቱ ሀብትን አከማችታችሁ ትገኛላችሁ፡፡

3
05/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 4 እንግዲህ ያደረጋችሁትን ነገር አስቡ፡፡ በእርሻችሁ ላይ ተገኝተው መከሩን ለሰበሰቡ ሰዎች ምንዳቸውን አልሰጣችሁም፡፡ ስለዚህም እነዚህ አጫጆች እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋል፤ ሁሉን ቻዩ አምላክ እግዚአብሔርም ደግሞ ከፍ ብሎ የተሰማውን ድምፃቸውን አድምጦአል፡፡
\v 5 የትኛውንም የምትፈልጉትን ነገር ገዝታችኋል፤ ስለዚህም እንደ ንጉሥ ትኖራላችሁ፡፡ ከብቶች ራሳቸውን እንደሚያደልቡና የሚታረዱ መሆናቸውን እንደማይገነዘቡ ሁሉ እንዲሁ እናንተም እግዚአብሔር እንደሚቀጣችሁ ባለመገንዘብ ነገሮችን በደስታ ለማጣጣም ኖራችኋል፡፡
\v 6 እነዚያ ሰዎች ጥፋት ባይፈጽሙም ንጹሐን ሰዎችን እንዲኰንኑ ሌሎችን አዘጋጅታችኋል፡፡ እነርሱ ራሳቸውን ከእናንተ መከላከል አይችሉም፡፡ ወንድሞቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ለሚጨቁኑዋችሁ ባለ ጠጎች የምላቸው ይህን ነው፡፡

2
05/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 7 እንግዲህ ወንድሞቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ባለ ጠጎች እንድትሰቃዩ ቢያደርጓችሁም ጌታ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ ታጋሾች ሁኑ፡፡ ገበሬዎች ተክልን ሲተክሉ ዋጋ ያለው ሰብል ለማግኘት የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትዕግሥት ይጠብቃሉ፡፡ መከሩን ከመሰብሰባቸው በፊት ሰብሉ እንዲያድግም ሆነ ተፈላጊው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ይጠብቃሉ፡፡
\v 8 እንዲሁ እናንተ በትዕግሥት ልትሆኑና ጌታ ኢየሱስን በጽናት ልትጠብቁ ይገባል፤ እርሱ ፈጥኖ ይመጣልና ደግሞም በሁሉም ሰው ላይ በቅንነት ይበይናል፡፡

3
05/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 9 9 እኅቶቼና ወንድቼ ሆይ፥ ጌታ ኢየሱስ እንዳይኰንናችሁም ሆነ እንዳይቀጣችሁ አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ አታጉረምርሙ፡፡ በእኛ ላይ የሚፈርድ እርሱ ነው፤ ሊገለጥም ደግሞ ዝግጁ ነው፡፡
\v 10 10 ወንድሞቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ታጋሽ መሆንን በተመለከተ ከረጅም ጊዜ በፊት መልእክቱን እንዲናገሩ እግዚአብሔር የላካቸውን ነቢያትን አስቡ፡፡ ሰዎች ብዙ እንዲሰቃዩ ቢያደርጓቸውም በትዕግሥት ጸኑ፡፡
\v 11 11 ስለ እርሱ መከራን የሚታገሡ ሰዎችን እግዚአብሔር እንደሚያከብርም ሆነ እንደሚረዳ እናውቃለን፡፡ ስለ ኢዮብም እንዲሁ ሰምታችኋል፡፡ ብዙ መከራን ቢቀበልም፣ መልካም ነገርን ሊያመጣለት እግዚብሔር ዐቅዷል፤ ያንን መከራ ታግሧልና፡፡ ከዚህም ደግሞ እግዚአብሔር እጅግ ሩኅሩኅና ደግ እንደ ሆነ እናውቃለን፡፡

View File

@ -69,6 +69,9 @@
"04-08",
"04-11",
"04-13",
"04-15"
"04-15",
"05-01",
"05-04",
"05-07"
]
}