am_hos_text_ulb/01/03.txt

1 line
634 B
Plaintext

\v 3 ስለዚህም ሆሴዕ ሄዶ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤እርስዋም ጸነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደችለት። \v 4 እግዚአብሔርም አለው፦ «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤል ስለነበረው ደም ማፍሰስ የኢዩን ቤት እቀጣለሁና፥ የቤተ እስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለ ሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው። \v 5 ይህም በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት በምሰብርበት ቀን ይፈጸማል።»