\v 4 የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ፥ ያለ መስፍን፥ ያለ መሥዋዕት፥ ያለ ድንጋይ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድ ወይም ያለ ቤተሰብ ጣዖት ለብዙ ቀናት ይኖራሉ። \v 5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሰዎች ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔር አምላካቸውንና ንጉሣቸውን ዳዊትንም ይፈልጋሉ። በመጨረሻዎቹም ቀናት በእግዚአብሔርና በበረከቱ ፊት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።